Tesfa Pre-Primary School
Announcement ዜና ተስፋ

ዜና ተስፋ

14th May, 2026



የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር በተስፋ ትምህርት ቤት ተካሄደ

[አዲስ አበባ — ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም]

በዛሬው እለት በተስፋ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ከጊብሰን እና ከመካኒሳ አባድር ትምህርት ቤቶች የመጡ መምህራንና የትምህርት አመራሮች በተገኙበት ውጤታማ የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ተካሄደ።

ይህ መርሃ ግብር በዋናነት ትኩረቱን በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት አሰጣጥ፣ በክፍል ውስጥ መማር ማስተማር ስልቶች እና በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ዙሪያ ያደረገ ነበር። በቆይታቸውም የትምህርት ቤቶቹን ምርጥ ተሞክሮዎች ለመቀመርና በትምህርት ጥራት ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችሉ ሰፊ ውይይቶች ተደርገዋል።

የተስፋ ትምህርት ቤት አመራሮች በእለቱ ባስተላለፉት መልእክት፣ መሰል የልምድ ልውውጦች በትምህርት ቤቶች መካከል ያለውን ግንኙነት ከማጠናከራቸውም በላይ፣ ለነገ ሀገር ተረካቢ ህፃናት የሚሰጠውን የትምህርት ደረጃ ከፍ ለማድረግ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።

መርሃ ግብሩ በታቀደው መሰረት በስኬት ተጠናቋል።


.

Copyright © All rights reserved.

Created with